በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ``ትውልድ በመምህር ይቀረፃል ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል!``በሚል ውይይት ተካሄደ።
Posted by admin on Saturday, 19 July 2025

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣ ግንቦት 15፣ 2017 ዓ.ም (ቡሆዩ)
በመድረኩ ላይ የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ፣የምዕራብ ጉጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አባል አቶ አዱላ ሂርባዬ፣የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ፣ም/ፕሬዝዳንቶች፣መምህራንና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይቱ ተካሂዳል ።
ለውይይት መነሻ ሀሳብ እንዲሆን በፌዴራል ደረጃ የተዘጋጀው ሰነድ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን ሰነዱንም የምዕራብ ጉጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዱላ ሂርባይ እና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ አቅርባል።
ሀገራዊ ለውጡ አሁን ያለበት ደርጃና ቀጣይ አቅጣጫዎች እንዲሁም የትምህርት ሰክተሩ አሁን ያለበት ሁኔታና ቀጣይ አቅጣጫዎች በሚል በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ በቀረበው ሰነድ ዙሪያ አሁን እየታዩ አበራታች ሥራዎችና በቀጣይም በመንግስት ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በመምህራን በኩል በርካታ አስተያየቶች ተሰጥቷል።
በተመሳሳይ መልኩ በትምህርት ሰክተሩ እየመጡ ላሉ ለውጦችና በቀጣይም ሀገር ተረካቢ ትውልድን በተሳካ ሁኔታ መቅረጽ እንዲቻል መስተካከል ባለባቸው ነጦቦች ዙሪያ አስተያየትና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በተለይ በአሁኑ ሰዓት መምህራን የኑሮ ውድነትን ተቋቁሞ በተረጋጋ ሁኔታ መሥራት እንዲችሉ የተለያዩ ስልቶች እንዲቀየሱ ጠይቋል።
በመጨረሻም ለተነሱት ጥያቄዎችም ሆነ አስተያየቶችየሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ፣የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አዱላ ሂርባይ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ ምልሽና ማብራሪያ ሰጥቷል።














































