በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ "አልረሳውም እኔም የኢትዮጵያ ወታደር ነኝ "
Posted by admin on Wednesday, 3 November 2021
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ "አልረሳውም እኔም የኢትዮጵያ ወታደር ነኝ!" በሚል መሪ ቃል በሰሜን እዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈፀመ የግፍ ተግባር ታስቦ ዋለ።
የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ዳርድንበር ከማስከበር ባሻገር ለአለም አቀፍ፣ ለአህጉራዊና ቀጠናዊ ሠላም መረጋጋትም የደም እና የህይወት ዋጋ በመክፈል ለሠላም ዘብ የቆመ የሀገር ደጀን ነዉ።
የሀገርን ድንበር እና ሉዓላዊነት ለማስከበር ከ20 ዓመታት በላይ የሀገርን ዳር ድንበር ሌት ተቀን ሲያስከብር በቆየው የሰሜኑ ዕዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ዘግናኝ እና ኢ-ሰብዓዊ የሆነ ጥቃት ተፈጽሟል።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲም ይህንን ቀን በማሰብና የሕይወት መስዋዕትነት ለከፈለውና እየከፈለ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደጀንነቱን ለማረጋገጥ ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም ከማለዳው 2:30 ጀምሮ በዩኒቨርስቲው ኦዳ አዳራሽ ፊት ለፊት መርሃግብሩን አካሂዷል።
በመርሃግብሩ ላይ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እና ተማሪዎች ተሳትፈዋል።
መርሃግብሩ ለ45 ሰከንድ የማሰብ ሥነስርዓት በማካሄድ ሻማ በማብራት ተከብሯል ።
"ኢትዮጵያ የዉስጥ ከሃዲዎችን እና የዉጭ ጠላቶቿን በተባበረ የዜጎች ክንድ ድል ትነሳለች!!!"
ለላቀ ለዉጥ እንተጋለን!!
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም