በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ ተካሄደ፡፡
Posted by admin on Thursday, 9 October 2025

መስከረም 22/2018 ዓ.ም :ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
በዩኒቨርሲቲዉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ መልክ የተመረጡት የመምህራን ማህበር ሥራ አስፈፃሚዎች ከተመረጡበት ጊዜ ወዲህ የተከናወኑትን ተግባራትና ሌሎችንም ጉዳዮች ጨምሮ የጉባዔዉ ተሣታፊ መምህራን በተገኙበት አቅርቦ ሰፊ ዉይይት ተካሂዷል፡፡
በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ፤ምርም፤ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህብረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬና የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አካሉ አሰፋ ተገኝቷል፡፡
በጉባዔዉ ላይ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ፤ምርም፤ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህብረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ የመምህራን አንድነት መጠናከር መብትና ግዴታቸዉን በማስከበሩ ረገድ ጉልህ ሚና ያለዉ ከመሆኑም ባሻገር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥም አስተወጽኦዉ ከፍተኛ ስለመሆኑ አስረድቷል፡፡
በዕለቱም የማህበሩ ፕሬዝዳንት መ/ር ብርሃኑ የማህበሩን የሦስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትን ጨምሮ የማህበሩ መሠረታዊ መተዳደሪያ ደንብ እና ማህበሩን ለማጠናከር በቀጣይ ለማከናወን የታቀዱ ዕቅዶችን አቅርቦ ዉይይቱ ተጠናቋል፡፡














































