በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ፡፡
Posted by admin on Tuesday, 17 December 2024
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሣሥ 02/2017 (BHU)
በዩኒቨርሲቲዉ የተካሄደዉ የጽዳት ዘመቻ የተቋሙን ማህብረሰብ በአጠቃላይ ያካተተ ሲሆን ‹‹አከባቢያችንን ከቆሻሻ አዕምሮኣችንን ከጥላቻ እናጽዳ›› በሚል መሪ ቃል እንድካሄድ የተደረገ ሲሆን የዩኒቨርሲቲዉን ቅጥር ግቢ በስድስት ዋና ዋና ቦታዎች በመከፋፈል ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎችን የማስወገድ ተግባር ተከናዉኗል፡፡
በዕለቱ የተደረገዉን የጽዳት ዘመቻ በማስመልከት የዩኒቨርሲቲዉ የአ/ምር/የቴክኖሎጂ ሽግግ/ማህ/አገ/ም ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ ጽዳት የመማር ማስተማር ሥራዉን አጋዥ ከሆኑ ነገሮች አንዱ መሆኑን በመጥቀስ የጋራ ቤታችንን በጋራና ቀጣይነት ባለዉ መልኩ በማጽዳትና ንጹህ ማድረግ አለብን ብሏል፡፡
በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲዉ አስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ነጌሳ ሞኮና የጽዳት ዘመቻዉ ምቹ የመማር ማስተማር አዉድ ከመፍጠሩም በላይ በጋራ የሚደረግ ተግባር የመንፈስ አንድነትን በማጠናከር እጅ ለእጅ ተያይዘን ችግሮቻችንን መፍታት የሚያስችል መሆኑን በመግለጽ በጽዳት ዘመቻዉ ለተሣተፉ ማህበረሰብ ምስጋና አቅርቧል፡፡