የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ሙያዎች ሲያሰለጥናቸዉ የቆየዉን ተማሪዎች ለ10ኛ ዙር አስመርቋል፡፡
Posted by admin on Thursday, 10 August 2023
ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ሙያዎች ሲያሰለጥናቸዉ የቆየዉን ተማሪዎች ለ10ኛ ዙር አስመርቋል፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ሙያዎች ሲያሰለጥናቸዉ የቆየዉን ተማሪዎች ለ10ኛ ዙር አስመርቋል፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን በቅርብ ጊዜ ከተቋቋሙት ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በ2004 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሥራዉን በመጀመር በዛሬዉ ዕለትም ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም ለ10ኛ ዙር በተለያዩ ሙያዎች ሲያሠለጥናቸዉ የቆየዉን በመጀመሪያ ድግሪ 907 ተማሪዎች በሁለተኛ ድግሪ 392 በድምሩ 1299 ተማሪዎችን የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍቃዱ ወ/ማርያምን ጨምሮ የምዕራብ ጉጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ አባል እንዲሁም የዕለቱ ክብር እንግዳ አቶ አዱላ ህርባዬ፤አቶ አህመድ አደም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምሪያ ኃላፊ፤የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንቶችና የሴኔት አባላት፤አባገዳዎችና የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች በተገኙበት በዩኒቨርሲቲዉ ዋና ግቢ ኦዳ አዳራሽ በደማ ሁኔታ አስመርቋል፡፡
**********ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ*********
**********ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ*********