የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሮኒክስ ባንኪንግ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡
Posted by admin on Wednesday, 17 November 2021
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሮኒክስ ባንኪንግ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡሌ ሆራ ቅርንጣፍ ጋር በመተባበር ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስ አስተዳደር ባለሙያዎች በኤሌክትሮኒክስ ባንኪንግ ጋር በተያያዘ ስልጠና ሰጠ፡፡
በስልጠናዉ ላይ ዶ/ር ታምሩ አኖሌ (የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ) ፣ዶ/ር ሮባ ደንቢ (የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ) እና ዶ/ር ጉሚ ቦሩ (የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት) ተገኝተዋል፡፡
የኤፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባወጣው አዋጅ መሰረት የፌዴራል ፋይናንስ ተቋማት ማንኛውንም ክፍያ በዲጅታል ኤሌክትሮኒክሲ የክፍያዎች መረብ መፈፀም እንዳለበት ይደነግጋል::
በዚሁ መሰረት የፋይናንስ አስተዳደር ደህነንትን ለመጠበቅ እና የፋይናንስ ዘርፉን ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤ እንዲሁም ለደንበኞች ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት እና እንግልትን ለመቀነስ ቴክኖሎጂዉ ጉልህ ሚና ስላለው ይህ ስልጠና ለዩኒቨሲቲዉ የፋይናንስ አስተዳደር ባለሙያዎች ተሰቷል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፋይናንስ ደህንነቱን ለመጠበቅ የባለሙያዎችን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎት ማዳበር ወሳኝ ጉዳይ መሆን እንዳለበት በስልጠናዉ ላይ ተጠቀሷል::
ይህ ስልጠና ፋይናንስ አስተዳደር ባለሙያዎች እየተሰጠ ከነበረዉ ስልጠና አካል ሆኖ ለሁለተኛ ቀን እራሱን ችሎ የተሰጠ ርዕሰ ጉዳይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ለላቀ ለዉት እንተጋለን!!!
07/03/2014 ዓ.ም
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ