በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነርንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና
Posted by admin on Tuesday, 2 August 2022
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነርንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለ1ኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ለሚማሩ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ። ሐምሌ 23፣ 2014ዓ.ም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ምክትል ዲን ኢንጂነር ዳስታ ጋማዳ ተማሪዎቹ ወደ ኮሌጁ ለመግባት ፍላጎታቸው እየቀነሰ መምጣቱን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ በአገር አቀፍ ደረጃ የፋብሪካዎች መስፋፋት እየጨመረ በመምጣቱ ሀገሪቱ ተጨማሪ ኢንጂነሮች ያስፈልጋታል ሲሉም ተናግረዋል።በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ አስራ ሁለት (12) ትምህርት ክፍሎች እንዳሉት እና አላማዎቻቸውንም ያብራሩት በኮሌጁ የአካዳሚክ ጥራት አስተባባሪ መ/ር ይድነቃቸው ዋዳአ እና የፕሪ እንጂነርንግ አስተባባሪ መ/ር ደራጄ አርጃሞ ናቸው።የስልጠናው አላማ ተማሪዎች ከአካዳሚክ ህይወት በኋላ የጥገኝነት አስተሳሰብ እንዳያዳብሩ እና ወደ ንግዱ አለም ገብተው በእውቀታቸው እንዲለወጡ ያላቸውን ግንዛቤ ማጠናከር ነው።በስልጠናው ላይ በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ስር የሚማሩ ብዙ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።ከተሳተፉት ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ እንደተናገሩት ይህንን ኮርስ ተምሬን ስራ አናገኝም ከማለት በሀገራችን በስፋት በሚገኙ የማዕድን ቁፋሮዎች ላይ ተማሪዎች የሚሳተፉበት ሰፊ የስራ እድል ተጠቃሚ መሆን ይገባናል ብለዋል።