የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኮሌጅ የጤና ባለሙያዎች 27ኛዉን የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በበየነ መረብ ተከታተሉ።
Posted by admin on Tuesday, 28 October 2025ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣ ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም (ቡሆዩ)
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት አመራሮችና ባለሙያዎች በጅማ ከተማ ''ዘላቂ ኢንቨስትመንት እና ኢኖቬሽን ለጠንካራ ጤና ሥርዓት '' በሚል መሪ ቃል የተካሄደውን 27ኛውን የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ በበይነ መረብ በቀጥታ ተከታትሏል።
በከተማዋ የተካሄደዉ ይህ ዓመታዊ ጉባኤ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሆን የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት አመራሮችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ባሉበት ሆነዉ ከጥቅምት 13-14/2018 ለሁለት ቀናት በበይነ መረብ ተከታትሏል ።


















































