በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የችግኝ ተከላና የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ።
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎች ፈተናዉን እንዳጠናቀቁ ሀገር አቀፍ የአረጉጓዴ አሻራ ፕሮግራምን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ዉስጥ የረሳቸዉን ድርሻ ለመወጣት በዩኒቨርሲቲዉ ግቢ ዉስጥ የተለያዩ ዛፎችን ተከሉ። በሀገር አቀፍ በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ የሆኑት የማሃበረዊ ሳይንስ ተማሪዎች በችግኝ ተከላዉ ላይ የተሳተፉ ሲሆን በተመሳሳስይ መልኩ በሚቀጠለዉ ሳምንት ለፈተናዉ የሚቀመጡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችም የአረንጓዴ አሻራዉን የማስቀጠልና የመተግበር ፕሮግራም እንደሚያካሂዱ ከወጣዉ ፕሮግራም ለመረዳት ተችሏል።
ይህንኑን አስመልክተዉ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ እንዲሁም የአካ/ምር/ተክ/ሽግ/ እና ማህ/አገ/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ትንሳኤ ታምራትና የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ነጌሳ ሞኮና የፈተናዉን አሰጣጥና ሂደትን አስመልክተዉ ባደረጉት ንግግር ፈተናዉ ያለምንም እንከንና ችግር ተጀምሮ የተጠናቀቀ በመሆኑ ፈተናዉን የሰጡትን መምህራንና ለፈተናዉ ሂደትና ስኬት የድርሻቸዉን የተወጡትን አካላት በማመስገን የምስጋና ፕሮግራሙን አጠቃለዋል።
በተጨማሪም በዩኒቨርሲቲያችን በመጀመሪያ ዙር የማህበረዊ ሳይንስ ተማሪዎችን የፈተኑ መምህራን የፈተናዉን ሂደተና አፈጻጸም አስመልክተዉ በዩኒቨርሲቲዉ በታየዉ መልካም የፈተና ስነ ምግባር የተሰማቸዉን ደስታ የገለጹ ሲሆን የምስጋና ፕሮግራሙንም አስመልክተዉ በተደረገዉ መልካም አቀባበልና መስተንግዶ መደሰታቸዉን ገልጸዋል።