ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት እና ግብርና ኮሌጅ ለተመለመሉ መምህራን ሥልጠና ተሰጠ፡፡
መስከረም 26/2017
`Integration of One health approaches and principles in to Teaching, Research, and Community services`በሚል ርዕስ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከግብርና ኮሌጅ ለተመለመሉ መምህራን ሥልጠና ተሰጠ፡፡
ሥልጠናዉ የተዘጋጀዉ `COHESA` Capacitating one Health In Eastern and Southern Africa` በሚል ድርጅት ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በሥልጠናዉ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ አመራሮችም ተገኝቷል፡፡
ዶ/ር ብርሃኑ ለማ ባደረጉት መክፈቻ ንግግር የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲም የድርጅቱ አባል ሆኖ በመቀላቀል በርካታ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን በመጥቀስ የተዘጋጀዉ ሥልጠና በአሁኑ ሰዓት የዓለም ህዝብ ቁጥር እጅግ በበዛበትና የሰዎች እንቅስቃሴ በጨመረበት ወቅት ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚመጡ በሽታዎችን በቅንጅት ለመከላከል አስፈላጊ ስለሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መዘጋጀቱ ተገቢ ና ወቅቱን የጠበቀ ሲሉ ተናግሯል፡፡
ዶ/ር ብርሃኑ አያይዘዉም በተለይም እንደእኛ አካባቢ የአኗኗር ዘይቤ የእንስሳትና የሰዎች ንክኪ በጣም የበዛበት መሆኑ ታዉቆ ከእንስሳት ወደሰዎች ሊተላለፉ የሚችሉ በሽታዎችን ከመከላከል አንፃር ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ በዚሁ ዙሪያም የተለያዩ ምርምሮችን የሚያደርጉ አካላትንም ዩኒቨርሲቲዉ የመደገፍ ሥራ እንደሚሠራ ተናግሯል፡፡
አሠልጣኞች፡-1.Professor ArgawAmbelufrom Addis Abeba University ,professor of environmental health and COHESA Team member. 2.D/r WaktoleYadeta Jima ,University COHESA Trainer Doctor Of Veterinary 3.D/r FufaAbunaAddis Abeba University Veterinary Medicine and COHESA Project Team Member.