በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሥረዓተ ትምህርት ክለሳ በኮፒዩቲንግና ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ተካሄደ።
Posted by admin on Tuesday, 17 December 2024
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 27/2017 ዓ.ም (BHU)
እንደሚታወቀው በመማር ማስተማሩ ሂደት የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠበቅና ብሎም ለማረጋገጥ ከሚተገበሩት ተግባራት አንዱና ዋናኛው ተዘጋጅቶ በሥራ ላይ ያለውን ሥረዓተ ትምህርት በየግዜው እንደ አስፈላጊነቱ በየደረጃው ባሉት የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ የሥረዓተ ትምህርት ክለሳና ፍተሻ ማድረግ ነው።
በዚሁ መሰረት በዩኒቨርሲቲው ካሉት ኮሌጆች አንዱ የሆነው የኮምፒዩቲንግ እና ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ በኮሌጁ እየተሰጡ ካሉት የ2ኛ ድግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች ዙሪያ የመማር ማስተማሩን ሥራ ዉጤታማ ለማድረግ የሥረዓተ ትምህርት ክለሳ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር አድርጓል ።
ይህን በማስመልከት የኮሌጁ ዲን መ/ር አሰፋ ሰንበቶ እንደተናገሩት የሥረዓተ ትምህርት ክለሳ ማድረግ የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ አንጻር ያለው ድርሻ ከፍተኛ ነው ብለዋል።በዚሁ መሠረት የሥረዓተ ትምህርት ክለሳ የተደረገባቸው የትምህርት ፕሮግራሞች መካከል :- "Msc in computer science, MSc in information technology, MSc in software engineering, Msc in data science " ናቸው።
በሥረዓተ ትምህርቱ ክለሳ ላይ ከተሳተፉት የትምህርት በለሙያዎች መካከል ሲኔር ስታፎች የነበሩበት ሲሆን በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ;ከአዳማ; ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ; ከባህር ዳር ዩኒቨርሳቲና እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሙሁራን ጭምር ሀሳባቸውን በበየነ መረብ እንዲያካፍሉ ወይም እንዲሰጡበት በማድረግ የሥረዓተ ትምህርቱ ክለሳ ወይም ፍተሻ እንድካሄድ ተደርጓል።