በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የዕቅድ ዝግጅት፤ክትትል;ግምገማና ሪፖርት አቀራረብን በተመለከተ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
Posted by admin on Friday, 17 January 2025

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም (BHU)
የአቅም ግንባታ ስልጠናዉ የተዘጋጀዉ በትምህርት ሚኒስቴርና በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የስትራቴጅክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ የጋራ ትብብር ሲሆን ሥልጠናው የተሠጠው ለኮሌጅ ዲኖች; ለዳይሬክተሮች; ለሥራ አስፈጻሚዎች; ለትምህርት ክፍሎችና ለአስተባባርሪዎች ነው።
የሥልጠናው ዋና ዓላማ በዕቅድ ዝግጅት፤ክትትል; ግምገማና ሪፖርት አቀራረብ ዙሪያ የሚስተዋለውን ክፍተትና የአቅም ውስንነት ችግሮችን በመቅረፍ የታዩትን ክፍተቶች ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ ስለመሆኑ ተገልጿዋል።
በሥልጠናዉ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ ሲሆኑ የስልጠናዉን አስፈላጊነት በሚመለከት መሠረታዊና ቁልፍ መልዕክቶችን ለሠልጣኝ ባለሙያዎቹ አስተላልፏል፡፡
ዶ/ር ብርሃኑ ባስተላለፉት መልዕክት በአሁኑ ወቀት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረጃ የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች እየተካሄዱ ከመሆናቸዉ ጋር ተያይዞ በተለያዩ የኃላፊነት መደቦች ላይ አዳዲስ አመራሮች እየመጡ በመሆናቸዉና እነዚህም አመራሮች ከሚያከናዉናቸዉ ወሳኝ ተግባራት መካከል የተቋሙን ራዕይ;ተልዕኮና የልህቀት ማዕከላትን "ባገናዘበ መልኩ ዕቅድ ማቀድ፤መተግበር፤ክትትል ማድረግና ተገቢዉን የሪፖርት ማጠናቀሪያ ፎርማት በመጠቀም የተሠሩ ሥራዎችን ሪፖርት ማድረግ የሚጠበቅ ተግባር በመሆኑ ይህንኑ ተግባር ለማከናወን እንዲያስችላቸዉ ታስቦ የአቅም ግንባታ ስልጠናው እንደተዘጋጀ ገልፀዋል፡፡
አያይዘዉም ፕሬዝዳንቱ ዕቅድ ስታቀድ የራሱ መነሻ ያሉት መሆኑን፤ከሀገርቷ ስትራቴጅክ ዕቅድ እየተመነዘረ የተቋሙን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ መሆን ስለሚገባዉ ሰልጣኞች ከሥልጠናዉ በሚገኘዉ ዕዉቀት በመጠቀም ለወደፊት የሚመለከታቸዉን አካላት በማሳተፍ ዕቅድ እንዲያዘጋጁና የትግበራ ጊዜ ሠላዳ በመጠቀም የታቀዱ ዕቅዶችን ወደ ተግባር መቀየሩ አስፈላጊና የሚጠበቅ የሥልጠናው ውጤት እንደሚሆን በአጽንኦት አንስቷል፡፡
በመጨረሻም ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት መልዕክት ተቋሙ ከመንግስት በሚበጀት በጄት የሚተዳደር እንደ መሆኑ መጠን የሚከናወኑ ተግባራት በሪፖርት መልክ ለተለያዩ መንግስት አካላት የሚላኩ ከመሆናቸዉ ጋር ተያይዞ የሚተገበሩ ሥራዎች ከዕቅዱ ጋር የተገናዘቡ ስለ መሆናቸዉ ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ተናግሯል፡፡
በተጨማሪ የዩኒቨርሲቲዉ ስትራቴጅክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሠለ አለማየሁ ለሥልጠናዉ መነሻ እንዲሆንም በሥራ ክፍሎች ደረጃ በእስካአሁኑ ሂደት በዕቅድ ዝግጅት፤ክትትል ;ግምገማና ግብረ መልስ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ያሉ ክፍተቶችን ካቀረቡ በኃላ ሥልጠናዉ ከትምህርት ሚኒስቴር በመጡ ባለሙዎች አማካኝነት በሁለት ምዕራፍ ተከፍሉ ተሰጥቷል፡፡
በዚሁ መሠረት ሥልጠናውን የሠጡት ከፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር ሁለት ባለሙያዎች ሲሆኑ በመጀመሪያዉ ምዕራፍ "Higher Education policy, Strategy and Legal Frame works , Ethiopian HE critical Challenges, Ethiopian Education reform Agendas እና Higher Education /Academic Leadership" በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ሲሆን;
በሁለተኛዉ ቀን ዉሎ ደግሞ "የዕቅድና የሪፖርት ጽንሰ ሀሳብ፤ዓመታዊ የዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት፤ በክትትልና ግብረ መልስ " አሰጣጥ ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን በእያንዳንዱ ሥልጠና ርዕስ መካከልም አስፈላጊዉን ዉይይት በማድረግና የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ስልጠናዉ ተጠናቋል፡፡