Research Methodology in Social Science: Quantitative and Qualitative research ``በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም (BHU)
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረጃ መምህራን ችግር ፈቺና ወቅታዊ የሆኑ የምርምር ሥራዎችን መሥራት ይችሉ ዘንድ ታሳብ ያደረገ በስነ-ሰብና ማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ አስተባባርነት በኮሌጁ ስር ካሉት የተለያዩ ኮሌጆች ለተመለመሉ መምህራን ለተከታታይ ሦስት ቀናት ተሰጥቷል፡፡
መምህራን የምርምር ችሎታቸዉን በማዳበር የማህብረሰቡን ችግር ልፈቱ የሚችሉ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በመሥራት ታዋቂ በሆኑ ጆርናሎች ላይ ጭምር ማሳተም እንዲችሉ በወሳኝ ደረጃ አጋዥ ከሆኑት መካከል የዳታ አሰባሰብና ትንተና መንገድ አንዱ ሲሆን የተቋሙን መምህራን አቅም ለማጎልበት ታስቦ የተዘጋጀ ስለመሆኑ መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን መ/ር ነጋሳ ገላና የገለፁ ሲሆን የዩኒቨርሲቲዉ ሪጅስትራርና አልሙናይ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዘርሁን ፈይሳም በሥልጠናዉ ቦታ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡
ሥልጠናዉ ጥራት ያላቸዉ የምርምር ሥራዎች አስፈላጊነት፤የዳታ አጠቃቀም ያላቸዉ ፋይዳ ፤የዳታ አሰባሰብ መንገድ፤የዳታ ትንተና የተገኙ ግኝቶችን ከመተንተንና በመሳሰሉ ተያያዥነት ባላቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ በጽንሰ ሀሳብ ሥልጠና ከመሰጠቱም ባሻገር የተለያዩ ሶፍትወሮችን በመጠቀም እንዴት ዳታን መተንተን እንደሚቻል በተግባር የተደገፈ ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ምርምር፤ስርፀትና ሥነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አብነት በቀለ በሥልጠናዉ መዝጊያ ዕለት ባስተላለፉት መልዕክት ከተሰጠዉ ሥልጠና ጥሩ ልምድ መገኘቱን፤ለቀጣይ ሥራም ጥሩ መደላድል የሚፈጥር መሆኑንና በቀጣይ በተቋማችን ደረጃ በሚሠሩ የምርምር ሥራዎች ላይ ጥቅም ላይ ይዉላሉ ያሉ ሲሆን የምርምር፤ስርፀትና ሥነ ምግባር ዳይሬክቶሬት በቅርበት በማህብረሰብና ስነ-ሰብ ሳይንስ ኮሌጅ ጋር ተባብሮ የሚሠራ ስለመሆኑ አንስቷል፡፡
ሥልጠናዉን የሰጡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ንጉሴ እና ዶ/ር አሸናፊ በላይ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ መሆናቸዉ ተገልጾዋል፡፡