በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የ”GAT”ፈተናና ምዝናን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

ሀምሌ 20/2016 ዓ/ም
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት ክዚህ በኋላ ትምህርታቸዉን በ2ኛና 3ኛ ዲግሪ መቀጠል ለሚፈልጉ መምህራን፣ ሌሎች የመንግስት ሰራተኞችና ግልሰቦች ማሟላት ከሚገባቸዉ መስፈርቶች አንዱ የሆነዉ የGAT(Graduation Admission Test) ፈተናና ምዘናን ወስዶ ማለፍ መቻል ነዉ።
በስልጠናዉ ላይ በመገኘት ስልጠናዉን በንግግርና ሃሳብ በመስጠት ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲዉ የአካዳሚክ፣ የምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ትንሳኤ ታምራት ናቸዉ። በንግግራቸዉ ካነሷቸዉ ሃሳብ አንዱ የጋት ፈተናን ወስዶ ማለፍ ከተቀመጠዉ አቅጣጫ ዋነኛዉ መስፈርት ሲሆን፣ እያንዳንዱ አመልካች ተማሪ ይሄንን ተገንዝቦ ስልጠናዉን በተኩረትና በመረጋጋት መዉሰድ እንዳለበት አስምረዉበት አሳስበዋል።

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ የማተማሪያ ሆስፒታል ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና አገልግሎት ተጠናቀቀ ።

ሀምሌ 17/2016 ዓ/ም

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታል ከሂማሊያን ካታራክት ፕሮጀክት (HCP) ጋር በመሆን ለአምስት ተከታታይ ቀናት የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ሲሰጥ ቆይቷል።በስራው ሂደት ካጋጠሙ የተለያዩ ክስተቶች መካከል አንዱ ከአንድ ቤተሰብ አምስት የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህሙማን የተገኙ ሲሆን፣ ለሁለቱ የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸዉ ማዬት የቻሉ ሲሆን ሶስቱ ህሙማን ግን ለተጨማሪ የህክምና እርዳታ ወደ ምኒልክ ሆስፒታል የተላኩ መሆናቸው ተገልጿል።  በተመሳሳይ መልኩ ሁለቱም ዓይኖቻቸዉ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ያለባቸው 115(አንድ መቶ አስራ አምስት) ህሙማን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና የተደረገላቸዉ ሲሆን፣በዚህ ዙር በአጠቃላይ በአምስቱ ቀናት ዉስጥ 621 (ስድስት መቶ ሃያ አንድ) ህሙማን የህክምና አገልግሎት ማግኘታቸዉ ተገልጿል።

የGAT(Graduate Admission Test) ስልጠና ለመውሰድ ለተመዘገባችሁ በሙሉ፣

ቀን 15/2016 ዓም
ማስታወቂያ

ስልጠናው የሚሰጠዉ ሀምሌ 19 እና 20/2016 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስለሆነ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በተጠቀሰዉ ቀን በግቢዉ በሚገኘዉ አባጡንጋ መታሰቢያ አዳራሽ በአካል ተገኝታችሁ ስልጠናውን እንድትከታተሉ እናሳዉቃለን።

Pages