የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በ2016ዓ/ም የ 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና (Entrance Exam)ለሚወስዱ ተማሪዎች ፈተና እየሰጠ ይገኛል።
Posted by admin on Tuesday, 30 July 2024በሀገር አቀፍ ደረጃ በወጣዉ መረሃ ግብር መሰረት ከሃምሌ 3/2016 ዓ/ም ጀምሮ ለሚሰጠዉ ፈተና ዩኒቨርሲቲዉ ሃምሌ 2/2016 ዓ/ም ለሁሉም ተማሪዎች ስለፈተናዉ አሰጣጥና የፈተና ዲሲፕሊን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ኦረንቴሽን የሰጠ ሲሆን፣ በተመሳሳይ መልኩ ፈተናዉን ለሚሰጡ መምህራንም አጠር ያለ ገለጻ ተሰቶአቸዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት ፈተናዉ ከጠዋቱ 3;00 እስከ 5;00 ሰዓት ሊሰጥ የተዘጋጀዉን የእንግሊዘኛ ቋንቋ የተሰጠ ሲሆን በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ ከ9;00 እስከ 12;00 ሰዓት የሚሰጠዉን የሂሳብ ትምህርት ተማሪዎች አየወሰዱት ይገኛሉ።