ከፌዴራል መንግስትና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የ2016 ዓ/ም የተማሪዎች የምርቃን አስመልክተዉ የተገኙት እንግዶች በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ የመስክ ምልከታ አደረጉ
Posted by admin on Tuesday, 30 July 2024ሰኔ 28/2016 ዓ.ም
ከፌዴራል መንግስትና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የ2016 ዓ/ም የተማሪዎች የምርቃን አስመልክተዉ የተገኙት እንግዶች በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ የመስክ ምልከታ አደረጉ፡
ከፌዴራል ገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር፣ከትምህርት ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የመጡት ፣የኦሮሚያ መስኖና አርብቶ አደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሮባ ቱርጬ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት የመስክ ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በመስክ ምልከታቸዉ ከመማር ማስተማሩ ጋር ተያያዥነት ባላቸዉ ጉዳዮች ዙርያ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን በሚመለከት ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማና ከዩኒቨርሲቲዉ አመራር አካላት ጋር በመሆን በግቢዉ በሚገኘዉ በሰርቶ ማሳያ የእርሻ ማሳ የመስክ ምልከታ አካሂደዋል፡፡