የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ካዉንስል በ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ዉይይት አካሄደ
Posted by admin on Wednesday, 22 June 2022የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ካዉንስል በ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ዉይይት አካሄደ
*****
በዉይይት መድረኩ ላይ በአገራዊ እና በተቋማዊ የ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ በተባባሪ ፕሮፌሰር ጫላ ዋታ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ የቀረበዉ የመነሻ ሀሳብ ጭብጦች፡ የ2015 ዓ.ም በአገራዊ የትኩረት አቅጣጫ አንኳር ጉዳዮች፤ የትምህርት ዘርፉን ቀጣይ አቅጣጫዎች ለምሳሌ፡-የትምህርት ጥራትና ተገቢነትን ማረጋገጥ፣ሌብነትንና ብክነትን መታገል፤ ፉትሃዊ ቅጥር፣ ምደባና አገልግሎት ማረጋገጥ፤ አካባቢያዊነትን መታገል፤ ፖለቲካና ትምህርትን መለየት-ሴኩላሪዝምን ማረጋገጥ፤ ራስ-ገዝነትን እና የቦርድ ሚና ማጠናከር ጥቂቶቹ ናቸዉ፡፡