የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ አደርገ::
Posted by admin on Friday, 4 February 2022የወሎ ዩኒቨርሲቲ በጦርነቱ ምክንያት ዉድመት ከደረሰባቸው ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ነው። በትምህርት ሚኒስቴር እና ኒቨርሲቲዎች በጋራ ጥምረት የተቋማቱን ጉዳት በመለየትና መልሶ ለማቋቋም ዩኒቨርሲቲዎች በሶስት ክላስተር ስር ተዋቅረዋል፡፡ በዚሁ መሰረት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ክላስተር ስር ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ አንዱ ሲሆን፤ለወሎ ዩኒቨርሲቲ መልሶ ማቋቋሚያነት ያግዛሉ የተባሉ ድጋፎችን አድርጓል፡፡ በመሆኑም ግምታዊ ዋጋቸው ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የቁሳቁስ ድጋፍ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ አስረክቧል።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የድጋፉ አስተባባሪ ኢንጅነር ጀማል ወርቁ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ጉዳት እኛንም ያሳስበናል በማለት በቻልነው አቅም ያለንን ለማካፈል መጥተናል ሲሉም ተናግረዋል ።