የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለዩኒቨረሲቲው በተለያየ ክፍል ባለሙያዎች እና የሰዉ ሀብት ልማት አስተዳደር ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።
Posted by admin on Monday, 22 November 2021የስልጠናው ትኩረት ከኦዲት ግኝት የፀዳ ተቋም ለመፍጥር በሚያስችሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲሆን፤ በገንዘብ ሚኒስቴር የኦዲት ኢንስፔክሽን ባለሙያ በአቶ መኮንን መኩሪያ ስልጠናው ተሰቷል።
የበጀት ክትትል፣ የተከፋይ ሂሳብ፣ የግዥ፣ የንብረት አያያዝና አጠባበቅ ስርዓት እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ የፋይናንስ አጠቃቀም እና አተገባበር የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች በስልጠናው ዉስጥ ተካተዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴርን ደንብ እና መመሪያ ህጉን በጠበቀ መልኩ የፋይናንስ ስርዓቱን ለማክበርና ለማስከበር በሚያስችሉ ፅንሰ ሀሳቦች ላይም ሰፊ ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል።