የመፅሀፍ ድጋፍ ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
Posted by admin on Friday, 12 November 2021የመፅሀፍ ድጋፍ ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
የኢትዮጲያ እውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማህበር ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የመፅሀፍ ድጋፍ አደረገ።
በድጋፉ የተበረከቱት መፅሀፍት ብዛት 231/ሁለት መቶ ሰላሣ አንድ/ ሲሆኑ፤ለህክምና ትምህርት የሚጠቅሙ ናቸውም ተብሏል። የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሰቲ የጤና ኢንስቲቲዩት ዲን መ/ር ታከለ ኡቱራ የተበረከቱት መፅሀፍት በኢንስቲቲዩት የሚስተዋሉትን የመፅሀፍት እጥረት ለመቅረፍ አጋዥነታቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል። መ/ር ታከለ ኡቱራ በሂደት ላይ ያለ የመፅሀፍ ግዥ እንዳለ አስታውሰዋል። እንደ ሜዲስንና አነስቴዥያን ያሉ ትምህርቶች የመፅሀፍት እጥረት እንደሚስተዋልባቸው ገልፀዋል።