የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለአትሌቶችን ምስጋናና የአንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ ።
Posted by admin on Thursday, 28 July 2022የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለአትሌቶችን ምስጋናና የአንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ ።
ሐምሌ 21/2014 (ቡሆዩ)የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለጀግኖች አትሌቶች በ18ኛው አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ከዕለም ሁለተኛ ከአፍሪካ አንደኛ ሆነዉ ድል ላስመዘገቡት የምስጋናና የአንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታምሩ አኖሌ (ፒኤችዲ) ባለፉት ጥቂት ዓመታት እንደ ሀገር ፈተና ያጋጠመን ቢሆንም ሳንደነቃቀፍ የኢትዮጵያን አኩሪ የድል ታሪክ መጻፍ የቻልን ትውልድ በመሆናችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ካዉንስል በ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ዉይይት አካሄደ
Posted by admin on Wednesday, 22 June 2022የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ካዉንስል በ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ዉይይት አካሄደ
*****
በዉይይት መድረኩ ላይ በአገራዊ እና በተቋማዊ የ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ በተባባሪ ፕሮፌሰር ጫላ ዋታ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ የቀረበዉ የመነሻ ሀሳብ ጭብጦች፡ የ2015 ዓ.ም በአገራዊ የትኩረት አቅጣጫ አንኳር ጉዳዮች፤ የትምህርት ዘርፉን ቀጣይ አቅጣጫዎች ለምሳሌ፡-የትምህርት ጥራትና ተገቢነትን ማረጋገጥ፣ሌብነትንና ብክነትን መታገል፤ ፉትሃዊ ቅጥር፣ ምደባና አገልግሎት ማረጋገጥ፤ አካባቢያዊነትን መታገል፤ ፖለቲካና ትምህርትን መለየት-ሴኩላሪዝምን ማረጋገጥ፤ ራስ-ገዝነትን እና የቦርድ ሚና ማጠናከር ጥቂቶቹ ናቸዉ፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ስብሰባ አካሄደ
Posted by admin on Tuesday, 3 May 2022የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት በ2014 ዓ.ም የ3ተኛ ዙር ስብሰባዉን በብሾፍቱ ከተማ ተቀመጠ፤ በመድረኩ ላይ አዲስ የቦርድ አባላት ተመድበው የሥራ ርክክብ አድርገዋል። እንዲሁም የዘጠኝ ወር የስራ እቅድ አፈፃፀም በመገምገም ለወደፊቱ የስራ አመራር በመስጠት ስብሰባቸው ተጠናቋል ።
አዲሱ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት
1. ዶ/ር ስዩም መስፍን-ሰብሳቢ
2. ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ -ምክትል ሰብሳቢ
3. ተባባሪ ፕሮፌሰር ጫላ ዋታ- ፀሃፊ
4. ፕሮፌሰር ገዛኸኝ ይርጉ -አባል
5. አቶ ጀምበሩ አበበ-አባል