የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በቡሌ ሆራ ከተማ ለሚገኙ የጽዳት እና የምግብ ዝግጅት ባለሙያዎች በተላላፊ በሽታዎች መከላከል ዙሪያ ስልጠና ሰጠ
Posted by admin on Monday, 29 November 2021የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በቡሌ ሆራ ከተማ ለሚገኙ የጽዳት እና የምግብ ዝግጅት ባለሙያዎች በተላላፊ በሽታዎች መከላከል ዙሪያ ስልጠና ሰጠ
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲው የጤና ኢኒስቲትዩት ጋጋር በመተባበር ባዘዘጋጀው ስልጠና ላይ ከ60 በላይ የሚሆኑ ሰልጣኞች ተሳትፈዋል።
ሰልጣኞቹ በጤና ተቋማት የሚሰሩ የጽዳት እና የምግብ ዝግጅት ባለሙያዎች ሲሆኑ፤ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል በሚያስችሉ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ በጤና ባለሙያዎች ስልጠናው ተሰጥቷቸል።
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የጤና ኢኒስቲትዩት፣ የምርምርና ማሕበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጅ ሽግግር ዳይሬክተር መ/ር ፍጹም ደምሴ እንደገለፁት 'ስልጠናው የጽዳትና የምግብ ዝግጅት ባለሙያዎችን እንዲሁም ተገልጋዮችን ለተላላፊ በሽታዎች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ለማድረግ የታሰበ ነዉ'።