የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለአትሌቶችን ምስጋናና የአንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ ።
Posted by admin on Thursday, 28 July 2022
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለአትሌቶችን ምስጋናና የአንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ ።
ሐምሌ 21/2014 (ቡሆዩ)የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለጀግኖች አትሌቶች በ18ኛው አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ከዕለም ሁለተኛ ከአፍሪካ አንደኛ ሆነዉ ድል ላስመዘገቡት የምስጋናና የአንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታምሩ አኖሌ (ፒኤችዲ) ባለፉት ጥቂት ዓመታት እንደ ሀገር ፈተና ያጋጠመን ቢሆንም ሳንደነቃቀፍ የኢትዮጵያን አኩሪ የድል ታሪክ መጻፍ የቻልን ትውልድ በመሆናችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል፡፡
ምስጋና በረከትና መትረፍረፍ የሚያመጣ በመሆኑ በማመስገን እና በጽናት በመጓዝ የበለጸገች ሀገርን ለመፍጠር እንሰራለን ነው ያሉት፡፡ ኢትዮጵያ በብዙ ፈተናና ውጣ ውረድ ብትፈተንም በፅናት ተቋቁማ ያገኘችውን ድል በማስመልከት ነው ለጀግኖች አትሌቶች የምስጋናና የአንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት የስተላለፉት፡፡
ለላቀ ለውጥ እንተጋለን
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ