የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሜዲስን ተማሪዎች ነጭ ጋዎን የመልበስ ቀን አከበሩ።

ህዳር 3/2016
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲቲዩት 4ኛ ዓመት የሜዲስን ተማሪዎችን ነጭ ጋዎን(ካባ) የመልበስ ቀንነ በደማቅ ሁኔታ ያከበሩ ሲሆን ተማሪዎቹ ከpre-clinical መማር ማስተማር ወደ clinical መማር ማስተማር የተሸጋገሩበትን 4ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ነው።  በዕለቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማን ጨምሮ የኢንስቲቲዩቱ መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል::
በፕሮግራሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የህክምና  ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሐሰን ቦኩ የህክምና ትምህርት ከፍተኛ የሆነ የግል ጥረት እንደሚፈልግ በመግለፅ ተማሪዎች የሚኖራቸውን ሙያ ለማሳደግ እና ጥሩ ሀኪም ሆኖ ለመገኘት መጣር እንዳለባቸው አሳስበዋል:: 

በኢትዮጵያ የUNFPA & KOICA ኃላፊዎች የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታልን ጎብኙ፡፡

ህዳር 01/2016 ዓ.ም 
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ከተለያዩ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የመግባቢያ ስምምነቶችን በመፈራረም በጤናው ዘርፍ አመርቂ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል፡፡
በመሆኑም የጋራ የሥራ ስምምነቱን በመፈፀም ከማስተማሪያ ሆስፒታሉ ጋር እየሠሩ ካሉ ድርጅቶች መካከል የUNFPA & Korea International Cooperation Agency (KOICA) ዋነኞቹ ሲሆኑ የድርጅቶቹ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች ልዑካን ቡድኖችን ጨምሮ በድርጅቱ ድጋፍ በማስተማሪያ ሆስፒታሉ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በድርጅቱ ድጋፍ የተቋቋመውን ማዕከል ጉብኝት የመሩት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የጤና ኢንስቲትዩት ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሳፋይ ኤለማ ናቸው። 

Pages