የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ልማት ማዕከል ወቅቱን ጠብቆ ስንዴ መዝራት መጀመሩን ገለፀ፡፡

ሚያዚያ 12/2015 ዓ.ም 
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ልማት ማዕከል ወቅቱን ጠብቆ ስንዴ መዝራት መጀመሩን ገለፀ፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ልማት ማዕከል በ2015 ዓ.ም ምርት ዘመን በሰላሳ ሄክታር የእርሻ መሬት ላይ ምርጥ ዘርና ግብዓት በመጠቀም ስንዴ መዝራት መጀመሩን አሳዉቋል፡፡የግብርና ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት መ/ር ሀሮ አዱላ እንደገለፁት የተዘሩት የስንዴ ዓይነቶች "ቀቀባና ኪንግ በርድ" የሚባሉ መሆናቸዉን በመጠቀስ ይህም በሄክታር ከ33-35 ኩንታል ምርት ሊገኝ እንደምችል ተናግሯል፡፡
መ/ር ሀሮ አያይዘዉም የእርሻ ሥራዉ ለዩኒቨርሲቲዉ በገቢ ምንጭነት ከማገልገሉም በላይ ለመማር ማስተማር ፤ለምርምርና ለማህብረሰብ አገልግሎት ከፍተኛ ጥቅም ያለዉ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይም በግብርና ልማት ማዕከል ሥር የተለያዩ የእርሻ ሥራዎችን በስፋት ለማከናወን እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ 
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በድርቅ ለተጎዱ  ለአካባቢው ማህበረሰብ 355 ኩንታል የስንዴ ምርጥ ዘር ማከፋፈሉን ገለፀ፡፡

ሚያዚያ 12/2015 ዓ.ም
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በድርቅ ለተጎዱ  ለአካባቢው ማህበረሰብ 355 ኩንታል የስንዴ ምርጥ ዘር ማከፋፈሉን ገለፀ፡፡
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ኢንተርፕራይዝ የተዘጋጀውን  በመግዛት  የስንዴ ምርጥ ዘር  ማከፋፈሉን ገልፀዋል፡፡የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍቃዱ ወ/ማርያም የተገዛውን  የስንዴ ምርጥ ዘር ለምዕራብ ጉጂ ዞን ም/አስተዳዳሪ ርክክብ ባደረጉት ወቅት እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲዉ የልህቀት ማዕከል አደርጎ ከሚሰራባቸዉ ሥራዎች አንዱ የግብርና ልማትን ማስፋፋት መሆኑን በመጥቀስ ይህ እየተከፋፈለ ያለዉ የስንዴ ምርጥ ዘር በአምስቱ ወረዳ ዉስጥ ላሉና በይበልጥ  በድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸዉ የህበረተሰብ ክፍል  መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይም ዩኒቨርሲቲዉ ተመሳሳይ ሥራዎችን በማህብረሰብ አገልግሎት በኩል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግሯል፡፡   

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የሥራ ዕቅድ ክንዉን ግምገማ ተካሄደ፡፡

ሚያዚያ 12/2015 ዓ.ም
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የሥራ ዕቅድ ክንዉን ግምገማ ተካሄደ፡፡
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የዕቅድ እና በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት አቅራቢነት የ2015 ዓ.ም የሦስተኛ ሩብ ወይም የዘጠኝ ወራት የሥራ የዕቅድ አፈፀፃም የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍቃዱ ወ/ማርያም እና የዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሪፖርት ቀርቦ ግምገማ ተደርጓል፡፡ 

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

ሰኔ 01/2015
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መውሰድ አለባቸው በሚል ትምህርት ሚኒስተር ያወረደውን መመሪያ መሠረት በማድረግ እና ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊው ሥራዎች እየተሠሩ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ስለሆነም እስከዛሬ በነበረው ሂደት አፈፃፀሙ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለመገምገም የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ እና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ከዩኒቨርሲቲው ኮሌጅ ዲኖች፣የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች እና ከየትምህርት ክፍሎች የተወከሉ የተማሪ ተጠሪዎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ

Pages