ጤና ኢንስቲትዩት ዕጩ ዶ/ር ዳዊት ገልገሎ እና ዕጩ ዶ/ር ሽፈራው ገልቹ የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት (phd) የመመረቂያ የምርምር ጽሑፋቸውን አቀረቡ።
Posted by admin on Saturday, 19 July 2025ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፣ ግንቦት 22፣2017 ዓ.ም (ቡሆዩ)
ዕጩ የሦስተኛ ዲግሪ(Phd) ተመራቂዎቹ የምርምር ሥራቸውን አዲቫይዜሮቻቸውን ጨምሮ የውጪ ገምጋሚዎችና ሌሎች ተጋባዥ ምሁራን በተገኙበት በማቅረብ በተሳካ ሁኔታ ጨርሰዋል።
በዕለቱም ዩኒቨርሲቲው በም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የጤና ኢንስቲትዩት ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሳፋይ ኤለማ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ዕጩ የሶስተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች ኢንስቲትዩቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያስመርቃቸው በመሆኑ ለኢንስቲትዩቱም ልዩ ቀን መሆኑን የገለፁ ሲሆን ተመራቂዎቹም በወጣትነት ዕድሜያቸውና በአጭር ጊዜ ለዚህ ስኬት የበቁበት መንገድ ለሌሎች አስተማሪና የይቻላል መንፈስን ያስተማረ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።