የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የክረምት በጎ አድራጎት ስራ በዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች አስጀመረ።
Posted by admin on Wednesday, 7 August 2024ሀምሌ 27/2016 ዓ/ም
የሰላም ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በ2016 በጀት ዓመት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሰጡ ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲዉ ደረጃ አሰልጥኗቸዉ የነበሩትን ተማሪዎች በማስተባበርና በመምራት የክረምት የበጎ አድራጎት ስራ /አገልግሎት/ እንዲሰጡ ከሀምሌ 27/2016 ጀምሮ የዩኒቨርሲቲዉን አጠቃላይ ቅጥር ግቢና የማስተማሪያ ሆስፒታል በማጸዳት አገልግሎቱን አስጀምረዋል። የበጎ አድራጎት አገልግሎቱን ለማስኬድ በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት የዩኒቨርሲቲዉ ክፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የዘመቻዉ አላማና ግብ በበጎ አድራጎት ስራ ላይ ለተሳተፉ ተማሪዎች ስፋ ያለ ገለጻ የተሰጠ ሲሆን፣የበጎ አድራጎት ስራዉም በቀጣይነት በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል በማዝመትና በመሰማራት እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።