“ማህበራዊ ትስስራችን ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችን'' በሚል መሪ ሃሳብ በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት የውይይት ተካሄደ።
Posted by admin on Thursday, 9 October 2025ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣ መስከረም፣ 2018 (ቡሆዩ)
“ማህበራዊ ትስስራችን ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችን'' በሚል መሪ ሃሳብ ሀገር አቀፍ የቃል-ኪዳን ቤተሰብ ማብሰሪያ የውይይት መድረክ በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት በአዳማ ከተማ ተካሂዷል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ እና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) የውይይቱ መድረክ ዓላማ ጎንደር ዩኒቨርስቲ የጀመረውን የቃል ኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት በሌሎች መንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙባቸው ከተማ አስተዳዳሪዎች በመውሰድና ዕቅድ በማውጣት ወደ ሥራ የገቡትን ለማበረታታት እና በይፋ ሥራው መጀመሩን ለማብሰር መሆኑን ተናግረዋል፡፡


















































