በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ``ትውልድ በመምህር ይቀረፃል ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል!``በሚል ውይይት ተካሄደ።
Posted by admin on Saturday, 19 July 2025ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣ ግንቦት 15፣ 2017 ዓ.ም (ቡሆዩ)
በመድረኩ ላይ የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ፣የምዕራብ ጉጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አባል አቶ አዱላ ሂርባዬ፣የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ፣ም/ፕሬዝዳንቶች፣መምህራንና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይቱ ተካሂዳል ።
ለውይይት መነሻ ሀሳብ እንዲሆን በፌዴራል ደረጃ የተዘጋጀው ሰነድ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን ሰነዱንም የምዕራብ ጉጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዱላ ሂርባይ እና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ አቅርባል።