የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኢንጅነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ሴሚናር-ዎርክ ሾፕ አካሄደ፡፡
Posted by admin on Friday, 17 January 2025ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 24/2017
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የሚያከናዉናቸዉን ተግባራትን በተመለከተ የጋራ ዓላማና ቀጣይነትን ባረገገጠ መልኩ ማስከድ እንዲቻል በ2017 የት/ዘመን ኮሌጁ ለማከናወን ካቀዳቸዉ አምስት ወርክ ሾፖች መካከል የመጀመሪያ ዙር በዛሬዉ ዕለት በኮሌጁ ስር ከሚገኙ ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ከተወጣጡ መምህራን ጋር ተካሂዷል፡፡
በወርክ ሾፑ ላይ ተገኝቶ መልዕክት ያስተላለፉት የኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ዲን መ/ር ቦሩ ቤደያ ሲሆኑ የወርክ ሾፑ ዋና ዓላማ በኮሌጁ ሥር ያሉ መምህራን የእርስ በርስ ልምድ ልዉዉጥ አድረገዉ የተሻለ ሥራ መሥራት እንዲችሉና በአሁኑ ሰዓትም እያንዳንዱ ትምህርት ክፍል የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሥራዎቻቸዉን ከማከናወን አንጻር ያሉበትን ደረጃ ለመፈተሽ አጋዥ መድረክ ስለመሆኑ አንስቷል፡፡